ሸሐዳ ለመያዝ ምስክር መጥራት ያስፈልጎታልን?
አንድ ሰው ሙስሊም ለመሆን ብሎ በእነገሌ ፊት እስልምናውን ያውጅ ዘንድ ግዴታ የለበትም። እስልምና በግለሰቡና በጌታው - ውዳሴና ልቅና ይገባው - መካከል ያለ ጉዳይ ነውና።
አንድ አዲስ ሰለምቴ መስለሙን እንዲመሰክሩለት ሰዎችን ቢጋብዝና ይህም በግል ዶሴዎቹ ውስጥ ተሰንዶ እንዲቀመጥለት ቢፈልግ፥ ይህ በራሱ ምንም ችግር የለውም። ነገር ግን ይህ ተግባር ሲፈፀም ለእስልምናው ተቀባይነት ማግኘት የግድ እንደሚያስፈልግ ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ መሆን አለበት።
ምንጭ:
islamqa.info
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed