እስልምና ግዳጅ ጋብቻዎችን ይፈቅዳል እንዴ?
ልጅህን ለልጄ የመሰጣጠት ጋብቻዎች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የተወሰኑ አገራት በስፋት የሚፈፀሙ ባህላዊ ልማዶች ናቸው። ምንም እንኳ ልማዱ የሙስሊሞች ብቻ ባይሆንም፥ ግዳጅ ጋብቻ በተሳሳተ መንገድ ከእስልምና ጋር ተያይዞ ይነሳል።
በእስልምና፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ውሃ አጣጭ ሊሆኗቸው የሚችሉ ሰዎችን የመምረጥ ወይም አልፈልግም የማለት መብት አላቸው፤ እናም ከጋብቻው ቀደም ብሎ እንስቲቱ እውነተኛ ፈቃደኝነቷን ያልሰጠችበት ጋብቻ ዋጋ የሌለውና ውድቅ ተደርጎ ነው የሚወሰደው።
ምንጭ:
islamicpamphlets.com
ትርጉም በ:
Abdu Ahmed