አንድ ሰው ሙስሊም የሚሆነው እንዴት ነው?

በፅኑ እምነት "ላ ኢላሃ ኢለሏህ፤ ሙሐመዱ ረሱሉሏህ" በማለት ብቻ አንድ ሰው በቀላሉ እስልምናን በመቀበል ሙስሊም መሆን ይችላል። ይህ አባባል "ከአሏህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም፤ ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ (ነብይ) ናቸው" ማለት ነው። "ከአሏህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም" የሚለው የመጀመሪያው ክፍል፥ ከአሏህ ውጪ ሌላ ማንኛውም አካል የመመለክ ስልጣን የለውም፤ እንዲሁም አሏህ አጋርም ሆነ ልጅ የለውም ማለት ነው። በተጨማሪም፥ አንድ ሰው ሙስሊም ለመሆን፥

  • ቅዱስ ቁርዓን አሏህ ያወረደው የራሱ ቀጥተኛ ቃል መሆኑን ማመን፤
  • አሏህ በቁርዓን ውስጥ ቃል እንደገባው፥ የመጨረሻው የፍርድ ቀን (ሙታን ከቀብር የሚቀሰቀሱበት ቀን) እውነት እንደሆነና እንደሚመጣ ማመን፤
  • እስልምናን ሐይማኖቱ/ቷ አድርጎ/ጋ መቀበል፤
  • ከአሏህ በቀር ምንንም እና ማንንም አለማምለክ፤ ይኖርበታል።

ነቢዩ ሙሐመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፡-

ከእናንተ አንዳችሁ፥ በምድረበዳ መሃል ጉዞ ላይ ሳለ ስንቅና መጠጡን እንደተሸከመች ጥላው የጠፋችበት ግመሉን መልሶ የማየት ተስፋው ጨልሞበት ዛፍ ስር ጥላ ላይ ተጋድሞ በሰመመን ሞቱን እየተጠባበቀ አይኑን ገለጥ ሲያደርግ በድንገት ግመሏን አጠገቡ ቆማ ቢያገኛት፥ ማሰሪያዋን በእጁ አፈፍ አድርጎ "ያ አሏህ፥ አንተ ባሪያዬ እኔ ደግሞ ጌታህ ነኝ" ብሎ ቢጮህ፥ ስህተቱ ከደስታው ብዛት የመነጨ ነው የሚሆነው። ከእንዲህ ያለው ሰው ይልቅ፥ ጌታዬ ይቅር በለኝ ብሎ ወደሱ በሚመለስ ተፀፃች አሏህ ይበልጥ ይደሰታል።

Sahih Muslim, 2747

ምንጭ: islam-guide.com
ትርጉም በ: Abdu Ahmed

ተመሳሳይ ጥያቄዎች